Uncategorized

ቢሾፍቱ! የቅርብ እሩቅ. . .

ወያኔ ከስሩ ተነቅሎ ከተቀበረ ቢሾፍቱ የተባለች የትውልድ መንደሬን ዳግም እንደማያት ከፍተኛ ተስፋ ነበረኝ።

ዳሩ ግን አልተሳካም።

የእድል ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም። አንዳንዱ ሳይዋጋ ጀግና – ሳይለፋ ሃብታም ይሆናል። ሌላው ደግሞ በተገላቢጦሽ። የእድል ጉዳይ ነው።

እነሆ! 1080 ኪሎሜትር ላይ ቁጭ ብዬ ቢሾፍቱን ከትካዜ ጋር እየናፈቅሁዋት ነው። ስለ ትውልድ መንደር ፍቅር ማወቅ የሚቻለው በመለየት ወቅት መሆኑ ግልጽ ነው። የእኔና የቢሾፍቱ ሃይቅ ፍቅር ግን ሚኻኢል ሾሎኮቭ ከዶን ወንዝ ጋር ካለው ቁርኝት እና ፍቅር እንኩዋ የላቀ ነው።

ተስፋ ግን አልቆረጥኩም። ይቺን ደባሪ ፕላኔት ተሰናብቼ ከመሄዴ በፊት ቢሾፍቱ ሃይቅ ዳርቻ ረጅም ሳቅ እስቃለሁ። ርግጥ ነው፣ ቢሾፍቱን ዳግም ለማየት እንቅፋት የሆነብኝ የልቤን ሁሉ እንደልቤ በመጻፌ መሆኑን አውቃለሁ። ይሄ ግን ተፈጥሮ ነው። ልለውጠው አልችልም።

ርግጥ ነው፣ በአካል ቢሾፍቱ ባልገኝም ብእሬ በየረር እና ከረዩ ሰማይ ስር እንደሚንሳፈፍ ወሬ አለኝ። ይህም የዘመናችን ምርጥ ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም “አገርን ሳይለቁ – ሌላ አገር መገኘት” ከሚለው ጋር ይመሳሰላል።

ስነጽሁፍ አስደሳች ነው። ቃላት ሃያል ናቸው። እንደ ንስር ሰማዩን ይቀዝፋሉ። እንዳ አሳ ባህሩን።

በቀጣይ በሚታተመው “ቀይ ዘመን” በተባለ መጽሃፌ ያደረግሁት ልዩ ነገር ቢኖር የመጨረሻው የብእር ነጻነት ላይ መድረስን ነው!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *